Fana: At a Speed of Life!

ለ32 ዓመታት ታግታ የነበረችው ሴት በመጨረሻም ከቤተሰቦቿ ጋር ተገናኝታለች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ለበርካታ ዓመታት ታግታ የነበረችው አርጀንቲናዊት ሴት በመጨረሻም ነፃ መውጣቷ ተነግሯል።

በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነበር በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ታግታ ደብዛዋ የጠፋው።

አሁን የ45 ዓመት ሴት የሆነቸው ይህች ታጋች ላለፉት 32 ዓመታት የት እንዳለች የማፈላለግ ስራ ሲሰራ ቢቆይም ምንም ፍንጭ ሳይገኝ ቆይቷል።

ሆኖም ግን ፖሊስ ከሰሞኑ አንድ አዲስ መረጃ ይደርሰዋል፤ የደረሰውን መረጃ ተከትሎ ሲሄድም ከ32 ዓመት በፊት ታግታ የጠፋቸው ሴት በደቡብ ቦሎቪያ ባርሜጆ እንዳለች ይደርስበታል።

በመጨረሻም ፖሊስ ታጋቿ የምትገኝበትን ቤት የመለየት ስራ ከሰራ በኋላ ታጋቿን እና የ9 ዓመት ወንድ ልጇን ከእገታ ነፃ ማውጣቱ ነው የተነገረው።

የአርጀንቲና ፖሊስ በሰጠው መግለጫም፥ ታጋቿ በመጨረሻም  ከቤተሰቦቿ ጋር መቀላቀሏን ይፋ አድርጓል፡፡

 

ምንጭ፦ www.bbc.com

You might also like
Comments
Loading...