Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ነገ በአዲስ አበባ ይከፈታል

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 21፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ)ሀገር አቀፍ የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ነገ በአዲስ አበባ ይከፈታል።

ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች የተውጣጡ ሞዴል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ኤግዚቢሽንና ባዛር በነገው ዕለት በአዲስ አበባ  የሚከፈት መሆኑን የፌዴራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አስታውቋል።

ኤግዚቢሽንና ባዛሩ “ተወዳዳሪ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በማፍራት የተጀመረውን ሃገራዊ ለውጥ እናፋጥናለን!” በሚል መሪ ቃል ከሰኞ እስከ እሁድ የሚካሄድ መሆኑ ነው የተገለፀው።

በዚህ ኤግዚቢሽንና ባዛርም  በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣በእንጨትና ብረታ ብረት፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በዕደ ጥበብ ስራዎች እና በሌሎች ዘርፎች ላይ የተሰማሩ አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን  ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

You might also like
Comments
Loading...