Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ የአሜሪካ ዶላር በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ያለውን የተጋነነ ሚና ነቀፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ በቻይና ጉብኝታቸው ዶላር ምንዛሪ እንዲሆን የወሰነው ማን ነው? ሲሉ  የአሜሪካ ዶላር መገበያያ መሆኑን ነቅፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በቻይና ይፋዊ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የአሜሪካ ዶላር በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ያለውን የተጋነነ ሚና በመንቀፍ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ላይ ተቃውሞ ሰንዝረዋል።

ሁሉም ሀገር ለንግድ ከዶላር ጋር መታሰር ያለበት ለምንድን ነው? ዶላር የዓለም  ገንዘብ እንዲሆን የወሰነውስ  ማነው? ሲሉም ሉላ የፖለቲካ አጋራቸው ዲልማ ሩሴፍ በብሪክስ አባል ሀገራት የተቋቋመው የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን  እውቅና ለመስጠት በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ተናግረዋል።

እንደ ብሪክስ ባንክ ያለ ባንክ በብራዚል እና በቻይና፣ በብራዚል እና በሌሎች የብሪክስ አባል ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ የሚደግፍ ገንዘብ ሊኖረው አይችልምን ሲሉም ጠይቀዋል።

አያይዘውም ዛሬ ሀገራት ወደ ውጭ ሸቀጦችን ለመላክ የራሳቸውን ገንዘብ ከመጠቀም ይልቅ ዶላርን ማሳደድ ግዴታ ሆኖባቸዋል ማለታቸውን አር ቲ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.