Fana: At a Speed of Life!

ጎግል ኩባንያ የደንበኞችን ግላዊ መረጃ ይፋ በማድረግ ቅሬታ እየቀረበበት ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል ኩባንያ የደንበኞችን ግላዊ መረጃ ይፋ በማድረግ እና የአውሮፓውያን የመረጃ ጥበቃ ህግ በመጣስ ቅሬታ እየቀረበበት መሆኑ ተገልጿል

በአስገዳጅ ደንበኞቹ የጎግል አቅጣጫ ተቋሚ እንዲጠቀሙ በማድረግ የሚገኙበትን አካባቢና ሌሎች ግላዊ ዝርዝር መረጃዎችን ከመስጠት ጋር በተያያዘ ቅሬታ እየቀረበበት መሆኑ ተነግሯል።

የተጠቃሚዎችን ሃይማኖት፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴ፣ ጤና ሁኔታና ሌሎች መረጃዎችን ሊሰጥ እንደሚችልም ነው የተገለጸው።

ቅሬታው የቀረበውም በጥናት ተደግፎ ሲሆን፥ 7 ድርጅቶች ቅሬታ ማቅረባቸው ታውቋል።

ከዚህ ባለፈም በኔዘር ላንድ፣ ሆላንድ፣ ግሪክ፣ ስሎቫኒያ፣ ሰዊድን እና ቼክ ሪፓፕሊክ የሚገኙ ድርጅቶች ቅሬታቸውን የማቅረብ እቅድ ያላቸው መሆኑ ተገልጿል።

ኩባንያው በበኩሉ አቅጣጫ ጠቋሚውን ማንኛውም ደንብኛ ሲፈልግ የሚጠቀመው ሳይፈልግ የሚዘጋውና የሚያስተካክለው መሆኑን አስታውቋል።

ይሁን እንጂ በየራሳችን ምርጫ የምንጠቀማቸው የእጅ ስልኮቻችን እና መተግበሪያዎች ከላይ የተጠቀሱት ግላዊ መረጃዎች ለመሰብሰብ እንደሚችሉ ጠቁሟል።

በቀረበበት ሪፖርት መሰረት አገልግሎቱን ለማሻሻልና በኩባንያው በኩል መሻሻል ያለባቸው ነገሮች ካሉ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል ተብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...