Fana: At a Speed of Life!

የወባ በሽታን ለመከላከል ከአራት ሚሊየን በላይ አጎበሮች ለተጠቃሚዎች እየተሰራጩ ነው

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የወባ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ከአራት ሚሊየን በላይ አጎበሮች ለተጠቃሚዎች መሰራጨት መጀመራቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአጎበር ስርጭቱም በሀገሪቱ ውስጥ የወባ በሽታ በስፋት የሚከሰተባቸው 134 ወረዳዎችን ማዕከል ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ህይወት ሰለሞን እንደገለጹት፥ በያዝነው በጀት ዓመት የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከ20 ሚሊየን በላይ የወባ መከላከያ አጎበር ግዢ መፈጸሙን ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓትም 4.4 ሚሊየን አጎበሮች በ134 ወባማ በሆኑ ወረዳዎች እየተሰራጩ መሆኑን የተናገሩት ዳይሬክተሯ ፥በቀጣይም ቀሪዎቹ አጎበሮች በታቀደላቸው ጊዜ  ወባማ በሆኑ ወረዳዎች መሰራጨት እንደሚጀምሩ ጠቁመዋል።

 

You might also like
Comments
Loading...