Fana: At a Speed of Life!

የመድሃኒት ሱስ የያዘው ግለሰብ በ10 ዓመት ውስጥ ከ30 ሺህ በላይ እንክብሎችን ውጧል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይናዊው ግለሰብ በያዘው የመድሃኒት ሱስ ምክንያት ሰሞኑን የቻይና መገናኛ ብዙሃን ላይ ርእስ ሆኗል።

ዋንግ የተባለው የ48 ዓመቱ ግለሰብ ከ10 ዓመት በፊት ያጋጠመውን የራስ ምታት ህመም ለማስታገስ ይረዳኛል በሚል ከገዛው የጉንፋን መድሃኒት ጋር ነው ሱስ የያዘው።

ዋንግ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ ሱሱን ለማስታገስ በሚል ከ30 ሺህ በላይ እንክብሎችን መዋጡ ነው እየተነገረ ያለው።

ዋንግ መድሃኒቱን ሳይውጥ የዋለ ቀን ምቾት እንደሚነሳው የገለፀ ሲሆን፥ ከዋጠው ግን ወደ ነበረበት ስሜቱ እንደሚመለስ ነው ያስታወቀው።

የመድሃኒት ሱስ የተጠናወተው ዋንግ ሱሱን ለማስታገስ በሚልም በየእለቱ ከ8 እስከ 12 ፍሬ እንክብል መድሃኒት እንደሚውጥም ነው የተናገረው።

አሁን ላይ የመድሃኒት ሱሰኝነቱ ወደ ከፋ ደረጃ እየሄደ ነው የተባለ ሲሆን፥ ህክምና ካላገኘ ለከፋ የጤና መታወክ ሊዳርገው እንደሚችልም ተነግሯል።

ዋንግ ገና ከአሁኑ ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት እና ምቾት የመንሳት ምልክቶች እየተስተዋሉበት መሆኑም ተነግሯል።

ምንጭ፦ www.odditycentral.com

You might also like
Comments
Loading...