Fana: At a Speed of Life!

አውስትራሊያና ቻይና በድጋሚ የቀረጥ ቅነሳ ለማካሄድ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣2011 (ኤፍቢሲ) አውስትራሊያና ቻይና በ2019 ተግባራዊ የሚደረግ የቀረጥ ቅነሳ ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ፡፡

እዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪስ ፓይን ወደ ቤጂንግ በማቅናት ከቻይና አቻቸው ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው ተብሏል፡፡

ወደ የሀገሮቻቸው በሚልኩዋቸው የተለያዩ ምርቶች ከላይ ከዚህ ቀደም ይጥሉት የነበረውን የ20 እና የ10 በመቶ ቀረጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚያነሱም ይጠበቃል፡፡

ሁለቱ ሀገራት የቀረጥ ቅነሳ ስምምነት ሲፈጽሙ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ከኢኮኖሚና ከንግድ ስምምነቶች በተጨማሪ የጋራ ጉዳዮች በሆኑ ሽብርተኝነትና የድህነት ቅነሳ ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪስ ፓይን ወደ ቤጂንግ ያቀኑት ከሁለት ዓመት በኋላ ነው ተብሏል፡፡

ሁለቱ ሀገራት መስከረም ወር ላይ የቀረጥ ቅነሳ ስምምነት ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2015 የቻይና አውስትራሊያ ነጻ የንግድ ስምምነት ወይንም ቻፍታን ማቋቋማቸው የሚታወስ ነው፡፡

 

ምንጭ፦ሲጂቲኤን

በአብርሃም ፈቀደ

You might also like
Comments
Loading...