Fana: At a Speed of Life!

ኒሳን የመገጣጠሚያ ማዕከሉን በጋና ሊከፍት ነው

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓኑ መኪና አምራች ኩባንያ ኒሳን በጋና የመኪና መገጣጠሚያ ማዕክል ሊከፍት መሆኑ ተገልጿል።

ኩባንያው በሀገሪቱ የመገጣጠሚያ ማዕከል ለመክፈት የሚያስችለውን ስምምነት ከጋና ንግድ ሚኒስቴር ሚኒስትር  ጋር መፈራረሙን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ሚኬ ዊትፊልድ ተናግረዋል።

ከስምምነቱ በኋላም የድርጅቱ ማዕከል የሚከፈትበትን ቦታ ለመምረጥ የመስክ ጥናት ማድረጋቸውን ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል።

ኒሳን ከዚህ በፊት በምዕራብ አፍሪካ  ናይጀሪያ ውስጥ ሌላ የመገጣጠሚያ ማዕከል ያለው ሲሆን ፥በጋና የሚከፍተው አዲሱ ማዕከልም በአካባቢው  ትልቁ የኒሳን መኪና መገጣጠሚያ ማዕከል ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ድርጅቱ ከመገጣጠሚያነት ባለፈ በምዕራብ አፍሪካ ትልቁን የሽያጭ ማዕከልም በጋና ውስጥ  የመክፈት ዕቅድ እንዳለው ሃላፊው አስታውቀዋል።

የጋና ንግድ ሚኒስቴር ሚኒስትር አላን ክዋዶው ኬሪማንተን በበኩላቸው ፥መንግስት ከኩባንያው ጋር የመገጣጠሚያ ማዕከሉን ለመክፈት የሚያስችል  ስምምነትመፈራረሙንና  የግንባታ ስራዉን ለማበረታታትም የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

በጋና የኢንዱስትሪው ዘርፍ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ገቢ ውስጥ 25 በመቶ የሚሆነውን የሚሸፍን ሲሆን ፥ይህን ገቢም በሚቀጥለው 2021 ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ሲጂቲኤን

You might also like
Comments
Loading...