Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ኩባንያ ሰዎችን በእንቅስቃሴ እና ቅርጽ ለመለየት የሚያስችል ሶፍትዌር ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት27፣ 2011 (ኤፍ.ቢሲ) የቻይና  ኩባንያ ሰዎችን በእንቅስቃሴ አና ቅርጽ ለመለየት የሚያስችል ሶፍትዌር ይፋ አደረገ።

ዋትሪክስ የተባለው የቻይና ኩባን የሰዎችን ማንነት በእንቅስቃሴ እና በሰውነት ቅርጽ ለመለየት የሚያስች ሶፍትዌር መስራቱን አርጋግጧል።

ኩባንያው የሶፍትዌሩን ውጤታማነትም በሳለፍነው ወር ቤጅንግ በሚገኘው ቢሮው ለእይታ ማቅረቡም ነው የተገለጸው።

94 በመቶ ያህል ውጤታማነቱ የተረጋገጠው ይህ ሶፍትዌር በሀገሪቱ የሳይንስ አካዳሚ ፈቃድ መሰጠቱም ተነግሯል።

ከ50 ሜትር ርቀት ላይ ፊታቸው የማይታይ ወይንም የተሸፈኑ ሰዎችን ከጀርባቸው በኩል በሰውነታቸው ቅረፃቸው ወይንም በእንቅስቃሴያቸው ለመለየት የሚያስችል መሆኑን የዋትሪክስ ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ ሁአነግ ዮንግዚን ተናግረዋል።

በፊት ገጽታ ማንነትን ለመለየት በሚያስችለው ቴክኖሎጂ ለመለየት የማይቻሉ ክስተቶች ሲፈጠሩ ክፍተቶችን በመሸፈን በኩል አዲሱ ሶፍትዌር የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው ተብሏል።

ቻይና በፊት ገፅታ ማንነት ለመየት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ በቤጅንግ እና ሻንጋይ ጎዳናዎች ላይ አገልግሎት ላይ ማዋሏ ተገለጿል።

ይሁን እንጂ የደህንነት ካሚራዎቹ የሚወስዷቸው ምስሎች ፊት የማያሳዩ እና የምስል ጥራት ችግር ሲያጋማቸው ማንነትን ለመለየት አስቸጋሪ የነበረ መሆኑ ተነግሯል።

አዲሱ የፈጠራ ውጤት እነዚህን ክፍተቶች በመሙላት በኩል ከፈተኛ ድርኛ እናዳለው ነው የተገለጸው።

በአዲሱ ቴክኖሎጂ ማንኛው መሳሪያ የተቀረጹ የምስል እና ድምጽ መረጃዎችን በማስገባት በ10 ደቂቃዎች ያህል ማንነትን ለመለየት የሚያስችል መሆኑም ነው በዘገባው የተመላከተው።

ቴክኖሎጂው የጃፓን፣ የብሪታኒያ፣ እና የአሜሪካ መከላከያ እና የመረጃ ተቋማት ከዛሬ አስር አመታት በፊት የደረሱበት ቢሆንም ለገበያ ያለማቅረባቸውን ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

ዋትሪክስ ኩባንያ ይህንን የቴክኖሎጂ ውጤት ለገበያ የማቅረብ ፍላጎት ያለው ሲሆን፥ ለዚሁ ተግባር 14ነጥብ5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልገውም ተነግሯል።

ምንጭ፦ abcnews

You might also like
Comments
Loading...