Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት ወደ ነበረበት ለመመለስ እየተሰራ ነው – ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት ወደ ነበረበት ለለመመለስ እየተሰራ  መሆኑን ፖሊስ ገለፀ።

በዞኑ ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት የክልሉ ፖሊስና የፌደራል የፀጥታ አካላት በቅንጅት አየሰሩ መሆኑን  የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘላለም ልጅዓለም ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አካባቢውን ወደ ነበረበት ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ ከአካባቢው ማሕበረሰብ፣ ከመንግስት አመራሮች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከወጣቶች ጋር በመተባባር እየተሰራ መሆኑ ነው የተገለፀው ።

ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር ባደረገው የተቀናጀ ስራም በአሁኑ ወቅት አካባቢው ወደ ነበረበት አንፃራዊ ሰላም መመለሱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ለተከሰተው ሁከትና ረብሻም በአሁኑ ወቅት የተፈጠረውን ለውጥ የማይደግፉ ሃይሎች ተጠያቂ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ስለሆነም  በሀገሪቱ የተፈጠረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለመቀየር የሚሰሩ አካላትን ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር በመተባባር የማያዳግም እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ተናግረዋል።

የአካባቢው  ማህበረሰብም ይህን አይነት ዕኩይ ተግባር በማውገዝ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።

በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ተሳትፈው የነበሩ ሀይሎች እና በተፈጠረው ሁኔታ ለዘረፋና ለተለያዩ ወንጀሎች ተሰማርተው የነበሩ የተወሰኑ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑ ተገልጿል።

በቀጣይም በጉዳቱ የጠፋው ንብረትና የሰው ሕይወት በባለሙያዎች ተጣርቶ ሲቀርብ ለማህበረሰቡ የሚገለፅ መሆኑን ከሚሽነር ዘላለም ተናግረዋል።

 

You might also like
Comments
Loading...