Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስ ብሪታኒያዊውን ስቴዋርት ጆን ሀልን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ ቀጠረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ አዲስ አሰልጣኝ መቅጠሩን አስታወቀ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ ብሪታኒያዊውን አሰልጣኝ ስቴዋርት ጆን ሀል መቅጠሩን ያውታወቀው።

አዲሱ አሰልጣኝ በነገው ዕለት ስራ የሚጀምሩ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ዋና ፀሀፊ፣ የቡድን መሪ እና ኮቺንግ ስታፍ ጋር ትውውቅ አድርገዋል።

የ62 ዓመቱ አሰልጣኝ አሰልጣኝ ስቴዋርት ጆን ሀል በሰጡት አስተያየትም፥ ቅዱስ ጊዮርጊስን ማሰልጠን እፈልግ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

“በተደረገልኝ ጥሪ መሰረት እድሉን ተጠቅሜ አሁን በርካታ ደጋፊዎች ባለቤት ወደ ሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ መጥቻለሁ በዚህም ደስተኛ ነኝ” ብለዋል።

አሰልጣኙ በቀደመው ጊዜ የበርሚንግሃም ሲቲ እግር ኳስ አካዳሚ ዳይሬክተር እና የተተኪ ቡድኑ እና ከ18 ዓመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝ የነበሩ ሲሆን በርሚግንሐምን ለቀው የህንዱን ፑኔ ሲቲን በአውሮፓውያኑ ከ2007-09 አሰልጥነዋል፡፡

በ2009 መጨረሻ ሴንት ቪንሰንት እና ግሬናዲያንስ ዋናውን እና ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት በመያዝ ከ20 ዓመት በታች ቡድኑን በኮንካካፍ ማጣሪያ ቡድኑን ከምድቡ አንደኛ በማድረግ ማሰለፍ ችለዋል።

አሰልጣኝ ስቴዋርት ጆን ሀል ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመምጣታቸው በፊት የባንግላዴሹን ሳይፍ ስፖርቲንግ ክለብ በማሰልጠን ለ18 ተከታታይ ጨዋታዎች ያለሽንፈት መጓዝ ችለዋል።

አሰልጣኙ የዩኤፋ የአሰልጣኛነትና የአሰልጣኞች አሰልጣኝነት ላይሰንስ ያላቸው መሆናቸውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አስታውቋል።

 

 

You might also like
Comments
Loading...