Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን ወደ ዋና ዋና ከተሞች ድረስ እንዲሸኟቸው አቅጣጫ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ሂደት ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እንዲቻል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ወደመጡበት አካባቢ እንዲሄዱ የሚል ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ከሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር በጉዞ እቅዳቸው ላይ የቪዲዮ ኮንፈረንስ አካሂዷል፡፡

ተሳታፊዎቹ የጉዞ አፈፃፀም እቅዶቻቸውንንና እስካሁን የደረሱበትን ሪፖርት አቅርበው አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

በዚህም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ጋር በመተባበር ጉዞውን እንዲያስተባብር ተወስኗል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎቻቸውን ወደ ዋና ዋና ከተሞች ድረስ እንዲሸኟቸው፣ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪ ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ በቀጣይ እንደ ሃገር ሊደረግ ለሚችለው ሃገራዊ ጥሪ ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ በተለይ የህክምና ተማሪዎች ያሏቸው ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ እንዲሁም የትምህርት ተቋማቱ ባሉበት ክልል ለሚደረግላቸው ማንኛውም ጥሪ መድረስ እንዲችሉ ዝግጅታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጧል።

እንዲሁም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከዩኒቨርሲቲዎች ወጥተው መሄድ ለማይችሉ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲዎች እንደየራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ የምግብ ቤት ሠራተኞችን አስገብተው እንዲያስተናግዱ እና በጉዞ ወቅት መኪኖችን ከማፅዳት ጀምሮ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲኖርና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ አቅጣጫ መሰጠቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.