Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው ያጋጠማትን ፈተና በመመከት ዛሬ ላይ አድርሰዋታል- አቶ ኦርዲን

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔር ብሔረሰቦች በአንድነት ኢትዮጵያ በየዘመኑ ያጋጠሟትን ፈተናዎች በመመከት ዛሬ ላይ አድርሰዋታል ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡

በሐረሪ ክልል 17ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በክልል ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

አቶ ኦርዲን በድሪ በአከባበሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ብሔር ብሔረሰቦች በአንድነት ኢትዮጵያ በየዘመኑ ያጋጠሟትን ፈተናዎች በመመከት ዛሬ ላይ እንድትደርስ አድርገዋል ብለዋል።

በቀጣይም በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን እና ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ብሔር ብሔረሰቦች የሀገር አንድነት እንዲጠበቅና ሰላም እንዲጎለብት እንደተባበሩ ሁሉ የሀገራችንን ብልፅግና እውን ለማድረግ እንዲረባረቡ መጠየቃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.