Fana: At a Speed of Life!

የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ መሰረት የተጠሪ ተቋማት ዝርዝር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አፅድቋል።

በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት የተጠሪ ተቋማትም በዝርዝር ቀርበዋል።

ለህዝብ ተወካዮች፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለሚኒስቴሮችና ለኮሚሽኖች ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል።

 1. ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

የፌደራል ሥነ ምግባርና ጽረ-ሙስና ኮሚሽን ናቸው።

 1. ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

የአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ

ቱሪዝም ኢትዮጵያ

የቤተ መንግስት አስተዳደር ናቸው።

 1. ለሰላም ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ

የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ

የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ

የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ናቸው።

 1. ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የሀገር መከላከያ ኢንጂነሪንግ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ

ጋፋት አርማመንት

ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ

ደጀን አቪየሽን ኢንጂነሪንግ

ብራና ማተሚያ ድርጅት

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዕቃዎች ማምረቻ ድርጅት ናቸው።

 1. ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት

የዲያስፖራ ኤጀንሲ ናቸው።

 1. ለገንዘብ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የመንግስት የልማት ድርጅቶች የዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ

የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ

የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ናቸው።

 1. ለጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ

የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር

የፍትህና የሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት

የሠነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ

የፌደራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ናቸው።

 

 1. ለግብርና ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

የግብርና ምርምር ካውንስል ሴክሬታሪያት

የህብረት ስራ ኤጀንሲ

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ

የቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን

የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች

የእንስሳት መድሃኒትና መኖ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን

ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ምርምርና ጥናት ማዕከል

የብሔራዊ ሰው ሰራሽ የእንስሳት ማራቢያ ዘዴ ማዕከል

የብሔራዊ የቆላ ዝንብና የገንዲ በሽታ መቆጣጠሪያና ማጥፊያ ኢንስቲትዩት

ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት ናቸው።

9 ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የስጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ማስፋፊያ ባለስልጣን

የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽ/ቤት

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስነ-ልክ ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ

የኢንዱስትሪ ግብዓት አቅራቢ ልማት ድርጅት ናቸው።

 1. ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከል ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያ ባዩቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት

የጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ናቸው።

11 ለትራንስፖርት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን

የማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት

የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን

የኢትዮ-ጂቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ትራንስፖርት አ.ማ

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት

የኢትዮጵያ ክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይ

12 ለከተማ ልማት ኮስትራክሽን ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የፌደራል ከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

የፌደራል ከተሞች የስራ እድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ

የተቀናጀ መሰረተ ልማት ማስተባበሪያ ኤጀንሲ

የኮንስትራክሽን ስራዎች ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት

የኮንስትራክሽ ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ናቸው።

 1. ለውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

 

የመስኖ ልማት ኮሚሽን

የውሃ ልማት ኮሚሽን

የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጄክት ጽ/ቤት

የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ብሔራዊ ሜትሪዮሎጂ ኤጀንሲ

የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ናቸው።

14 ለማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ

የኢትዮጵያ የገጠር ኢነርጂ ልማት ማስፋፊያ ማዕከል

የኢትዮጵያ ነዳጅና ጋዝ ምርትና አቅርቦት ኮርፖሬሽን ናቸው።

 1. ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ናቸው።

 1. ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂክ ማዕከል

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ

የፌደራል ቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ኢንስቲትዩት

የፌዴራል ቴክኒክና ትምህርት ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት

17 ለጤና ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

ቅዱስ ጴጥሮስ ቲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታልና ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ

ቅዱስ አማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

የመላ አፍሪካ ስጋ ደዌ መከላከያና ትምህርት መስጫ ማዕከል

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

የመድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ

የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ

ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት

የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት

ብሔራዊ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ናቸው።

18 ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን

የብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት ኤጀንሲ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

የሆቴሎችና ቱሪዝም ስራ ማሰልጠኛ ማዕከል

ስፖርት ኮሚሽን ናቸው።

 1. ለገቢዎች ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የጉምሩክ ኮሚሽን

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ናቸው።

 1. ለፕላንና ልማት ኮሚሽን ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ናቸው።

 1. ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ

መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ

የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት

የኢትዮጰያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት

የመንግስት ሰራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ናቸው።

22. ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን

የመሬት ልማት ባንክ ኮርፖሬሽን ናቸው።

23. ለአካባቢ ጥበቃ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የኢትዮጵያ ብዝሃ-ህይወት ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያ አካባቢና ደን ምርምር ኢንስቲትዩት

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ናቸው።

የውሃ ልማት ፈንድ ተጠሪነት ለውሃ ልማት ኮሚሽን ሆኗል።

24 ለስፖርት ኮሚሽን ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል

ጸረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት ናቸው።

 

You might also like
Comments
Loading...