Fana: At a Speed of Life!

የስሎቬንያው ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የስሎቬንያ ፕሬዚዳንት ቦሩት ፓሆር ከመጭው ሰኞ ጀምሮ በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ።

በጉብኝታቸው ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር እንደሚወያዩም ነው የሚጠበቀው።

ጉብኝቱ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ለማጠናከር ያለውን የጋራ ፍላጎት የሚያሳይ ነው መባሉን፥ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like
Comments
Loading...