Fana: At a Speed of Life!

ወጣቱ ለሁለንተናዊ የሀገር ግንባታ ለሚደረገው ጥረት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቱ ለሁለንተናዊ የሀገር ግንባታ ለሚደረገው ጥረት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
 
ለአምስት ቀናት የሚቆይ የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ስብሰባ በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
 
ትውልዱ የሀገር ባለቤት በመሆኑ ለወቅቱ የሀገሪቱ ችግር መፍትሄ ሊሆን ይገባልም ነው የተባለው ።
 
ጭር ሲል የማይወዱና ሰላምን የሚፃረሩ ሀይሎችን በመቃወም በጋራ መቆም እንደሚገባም ተገልጿል፡፡
 
ሀገርን ከመገንባቱ ጎን ለጎን ወጣቱን ስራ ላይ ማሰማራት በዞኑም ሆነ በክልል ደረጃ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑ ተጠቁሟል።
 
በአቤኔዘር ታዬ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.