Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጣሊያን የ696 ሚሊየን ብር የብድርና ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያና ጣሊያን የ538 ሚሊየን ብር ብድርና የ158 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት  በዛሬው ዕለት ተፈራረሙ።

የእርዳታና ይድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስትር ደኤታ አቶ አድማሱ ነበበና ኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አርቱሮ ሉዚ ተፈራርመዋል።

ብድሩና ድጋፉ በከተሞች  የንፁህ ውሃ አቅርቦትና የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድን ለማማሻሻል የሚውል ነው ተብሏል።

ሥምምነቱ በኢጣሊያ የልማት ትብብርና በውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር በጋራ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተነግሯል።

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለከስጥናት ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም ይጠበቃል።

በውይይታቸውም፥በሁለትዮሽ፣ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩና የተለያዩ የሁለትዩሽ ስምምነቶች እንደሚፈራረሙም ይጠበቃል።

You might also like
Comments
Loading...