Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ባህርዳርና ጅማ አባ ጅፋር ድል ቀናቸው

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በ9 እና 11 ሰዓት ከ20 ተጋባዥ የክልል ክለቦች እርስ በእርስ የተገናኙበትን ሁለት ጨዋታ ተካሂደዋል።

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዛሬው ዕለት በተካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ባህርዳር  ከተማና ጅማ አባ ጅፋር  ተጋጣሚዎቻቸን በተመሳሳይ 1 ለ 0 በመሆነ ውጤት አሸነፈዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በ9 እና 11 ሰዓት ከ20 ተጋባዥ የክልል ክለቦች እርስ በእርስ የተገናኙበትን ሁለት ጨዋታ ተካሂደዋል።

ጀማ አባ ጅፋር ከወላይታ ድቻ  9 ሰዓት ላይ በተገናኙበት ጨዋታ  አስቻለው  ግርማ በ59ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ  ጅማ  አባ ጅፋር 1 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል።

በሌላ ጨዋታ በዘንድሮ ዓመት ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለው ባህርዳር ከተማ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 በማሸነፍ በአዲስ አበባ ዋንጫ ሁለተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በጨዋታው ጃኮ አራፋት  29 ደቂቃ ባህርዳር ከተማን አሸናፊ ያደረገችውን ሲያስቆጥር ፋሲል ከነማዎች ያገኙትን የፍጹም ቅጣት ምት ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል።

ወንድሜነህ ደረጄ ከባህር ዳር ከተማና  ከአስቻለው ግርማ ከጅማ አባ ጅፋር  የጨዋታዎቹ  ኮከብ በመሆን መመረጥ ችለዋል።

You might also like
Comments
Loading...