Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ባህር ዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎችን አስተናግዷል።

በዛሬው እለት ባህር ዳር ከተማ ከወላይታ ዲቻ እንዲሁም ፋሲል ከነማ ከጅማ አባ ጅፋር ተገናኝተዋል።

ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ወላይታ ዲቻን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ጎሎቹንም ኤልያስ አህመድ እና ጃኮ አራፋት አስቆጥረዋል።

በሌላ ጨዋታ ደግሞ ፋሲል ከነማ ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል።

ለፋሲል ከነማ ኢዙ ኦዛካ ሁለቱን የድል ጎሎች ሲያስቆጥር ቢስማርክ አፒያ ደግሞ የጅማ አባ ጅፋርን ጎል አስቆጥሯል።

You might also like
Comments
Loading...