Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ኢትዮጵያ ቡና እና ባህርዳር ከተማ የፍጻሜ ተፋላሚ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 7 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎችን አስተናግዷል።

9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ መከላከያ ከተጋባዡ ባህር ዳር ከተማ ተገናኝተዋል።

ጨዋታውን ባህር ዳር ከተማ 3 ለ 2 ሲያሸንፍ፥ ፍቅረሚካኤል ዓለሙ፣ ግርማ ዲሳሳ እና ማራኪ ወርቁ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

አዲሱ ተስፋዬ እና አቅሌሲያስ ግርማ ደግሞ የመከላከያን ሁለት ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል።

ማምሻውን በተጀመረ ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ለኢትዮጵያ ቡና ሁለቱን ግቦች ቶማስ ስምረቱ እና አቡበከር ነስሩ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ አስቆጥረዋል፡፡

የጅማ አባ ጅፋርን ብቸኛ ግብ አስቻለው ግርማ በሁለተኛ አጋማሽ የመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ አግብቷል፡፡

በዚህም ቅዳሜ በ9 ሰዓት መከላከያ ከጅማ አባ ጅፋር ለደረጃ ሲጫወቱ ፥ ባህር ዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና 11 ሰዓት ላይ ለዋንጫ ይፋለማሉ፡፡

 

 

You might also like
Comments
Loading...