Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ቱርክ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በመስመጧ 8 ሰዎች ሲሞቱ 25ቱ የደረሱበት አልታወቀም

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 01፣2011(ኤፍ ቢ ሲ)በምስራቅ ቱርክ ኢዝሚር ግዛት በደረሰ የጀልባ መስመጥ አደጋ የ8 ሰዎች ህይዎት ሲያልፍ 25 ስደተኞች መጥፋታቸው ተገለፀ፡፡

የቱርክ የባህር በር ጠባቂዎች እንዳስታወቁት ፥ በምስራቅ ቱርክ ባህር ዳርቻ ስደተኞችን በመጫን ሰትጓዝ የነበረች ጀልባ በመስመጧ 8 ሰዎች ሲሞቱ 25 ቱ የደረሱበት አለመታቁን ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላ 35 ስደተኞችን አሳፍራ ትጓዝ የነበረቸው ጀልባ መነሻዋም ሆነ መድረሻዋ እስካሁን አለመታውቁም ተገልጿል፡፡

የጀልባዋ የተለያ የአካል ክፍሎች ውሃ ማስገባታቸው ለጀልባዋ መስመጥ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር የተገለፀ ሲሆን ፥ በአደጋው የጠፉትን ሰዎች የማፈላለጉ ሂደትም እንደቀጠለ ነው ፡፡

በአደጋው የጠፉ ሰዎችን ለማፈላለግም አንድ ሄሊኮፕተር ፣አንድ አውሮፕላንና ሶስት ጀልባዎች የተመደቡ ሲሆን ፥ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም ስደተኞችን የማፈላለጉን ስራ እያሳለጡ ይገኛሉ፡፡

ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በሚሊየን የሚቆጠሩ ስደተኞች የተሻለ ኑሮን ፍላጋ ወደ አውሮፓ ለመግባት የቱርክ ባህርን እንደመተላለፊያ መስመር ይጠቀማሉ፡፡

በዚህ የጉዞ መስመር በፈረኝጆቹ 2016 በደረሰ አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች መሞታቸዉን ተከትሎ፥ ቱርክ በጉዳዩ ዙሪያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ባደረገችው ስምምነት ስደተኞች በመስመሩ የሚያደረጉት ጉዞ መግታት መቻሉ ተጠቅሷል፡፡

ምንጭ፡- http://english.ahram.org.eg

 

 

You might also like
Comments
Loading...