Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከቻይናው አምባሳደር ታን ጂያን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ጥቅምት 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከቻይናው አምባሳደር ታን ጂያን ጋር ተወያዩ።

ምክትል ከንቲባው በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ከአምባሳደር ታን ጂያን ጋር መክረዋል።

በዚህም በከተማዋ የሰው ሀይል ስልጠና፣ በኢንቨስትመት እና በቱሪዝም መስኮች ላይ በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ነው የተገለጸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች ቻይና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗንም የቻይናው አምባሳደር ታን ጂያን አረጋግጠዋል።

You might also like
Comments
Loading...