Fana: At a Speed of Life!

ጃዋር መሀመድ በመጪው እሁድ ከድሬደዋ ከተማ  ነዋሪዎች ጋር ይወያያል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና አክቲቪስት ጃዋር መሃመድ ከነገ በስቲያ  ከድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ተገለፀ።

ለጃዋር ሙሀመድ በድሬደዋ ከተማ የሚደረገው አቀባበልና ውይይት  በሰላም  እንዲጠናቀቅ የጸጥታ ሃይሉ  ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌታቸው አስረስ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ አቀባበሉና ውይይቱ በሰላም ለማጠናቀቅ  አስፈላጊው ዝግጅት እንደተደረገ ነው ያስታወቁት።

ከዚህ ባለፈ በትናትናው እለት በድሬደዋ ከተማ አቀባበል የተደረገለት የሰብአዊ መብት ተሟጋችና አክቲቪስት አርቲስት ታማኝ በየነ በሰላም መጠናቀቁን ኮሚሽመነሩ ተናግረዋል።

በፍቅርና በመከባበር ተምሳሌት የሆነው የድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች ላሳዩት ሰላማዊ ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል።

በታሪክ አዱኛ

 

You might also like
Comments
Loading...