Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በክብር እንዲሰናበቱ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ጉባዔውን ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በክብር እንዲሰናበቱና ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ባይወዳደሩ ሲል ስያሜውን ዛሬ ወደ አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) የቀየረው ብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ የድርጅታዊ ጉባዔውን ጠየቀ።

ማእከላዊ ኮሚቴው ያቀረባቸው በትምህርት፣ በአምባሳደርነት እና በክብር የሚሰናበቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሚል ነው።

በዚህም መሰረት፦

በክብር

አቶ ደመቀ መኮንን

አቶ ከበደ ጫኔ

አቶ መኮንን የለውምወሰን

ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው

አቶ ጌታቸው አምባዬ

በትምህርት

አቶ ዓለምነው መኮንን

አቶ ለገሰ ቱሉ

አቶ ጌታቸው ጀምበር

አቶ ኢብራሂም ሙሀመድ

አቶ ደሳለኝ አምባው

ወይዘሮ ባንቺይርጋ መለሰ

በአምባሳደርነት እያገለገሉ ያሉ

አቶ ካሳ ተክለብርሃንና

ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ ናቸው።

ከላይ የተዘረዘሩት ነባር አመራሮች ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የማይወዳደሩት እና በክብር የሚሰናበቱት 12ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ከተስማማባቸው እና ከወሰነ ብቻ ነው።

ድርጅታዊ ጉባዔው በነገው እለትም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን፥ የድርጅቱን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር፣ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እና የስራ አስፈፃሚ አባላት ምርጫን አካሂዶ በነገው እለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

 

በዳዊት መስፍን

You might also like
Comments
Loading...