Fana: At a Speed of Life!

በኢንዶኔዥያ ሳውሉሲ ደሴት የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ800 በላይ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢንዶኔዥያ ሳውሉሲ ደሴት ፓሉ ከተማ በባሳለፍነው አርብ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ800 በላይ መድረሱ ተገለፀ።

7.5 ሬክተር ስኬል መጠን ያስመዘገበው ይህ የመሬት መንቀጥቀጥአደጋ፥የሰዎቹን ህይዎት ከመቅጠፍ ባለፍ የከተዋማን በርካታ ሕንፃዎች ማፈራረሱ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅትም በርካታ ሰዎች በህንፃዎች ፍርስራሽ ስር እንደሚገኚ የነገረ ሲሆን እስካሁንም በትንሹ የ832 ሰዎች ህይወት በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ሞተዋል ነው የተባለው።

የኢንዶኔዥያ ድንገተኛ አደጋ ጊዜ ተጠሪ ቃል አቀባይ ሱቶፖ ፑርዎ እንደገለፁት፥ በሀገሪቱ በሚገኙ አራት ሆስፒታሎች ዉሥጥ ተጎጅዎች እርዳታ እየተደረገላቸዉ መሆኑንና የጠፉ ሰዎችን በፈራረሱ ሕንፃዎች ሥር የማፈላለጉ ሂደት መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

ቃል አቀባዩ እስካሁን ባላቸዉ መረጃ የሟቶች ቁጥር በትንሹ 832  የደረሰ ሲሆን የተጎጅዎች ቁጥርም እየጨመረ መሄዱን አብራርተዋል፡፡

በመሬት መንቀጥቀጥ  የተፈጠረው የሱናሜ አደጋ የመገናኛ አውታሮችንና መሰረተ ልማቶችን በማውደሙ ፥የተጎጅዎችን ህይዎት ለማትረፍ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በጥምረት የመስራቱን ሒደት አስቸጋሪ ማድረጉን ሀላፊው ተናግረዋል።

የኢንዶኔዥያው ፕሬዘዳት ጃኮ ዊዶዶ አደጋውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ  ከአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በተጨማሪ ለሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት  በከተማዋ የተጎዱ ሰዎችን ለመታደግና የጠፉ ሰዎችን ለማፈላለግ ጥሪ ማደገራቸዉን አስታውቀዋል።

በአደጋዉ ለተጎዱ ሰዎች የሚያስፈልጉ የተለያዩ የእርዳታ ዕቃዎችም በፍጥነት ወደ አካባቢዉ እንደሚደርሱፕሬዘዳንቱ ተናግተረዋል።

በኢንዶኔዥያ የመሬት መንቀጥቀጥ በብዛት የሚከሰት ሲሆን፥ባለፈዉ ነሐሴ ወር ሎምቦኮ በምትባል ደሴት በአደጋዉ 500 ባለይ ሰዎች መሞታቸዉ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like
Comments
Loading...