Fana: At a Speed of Life!

ህወሃት የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫና የ12 ነባር አመራሮችን ስንብት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 5ኛ ቀኑን የያዘው የህውሃት ድርጅታዊ ጉባዔ በዛሬ ውሎው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ድርጅታዊ ጉባዔው በዛሬው ውሎው የማእከላዊ ኮሜቴ አባላት ምርጫ ያካሄደ ሲሆን፥ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ቁጥርም ከ45 ወደ 55 ከፍ እንዲል ወስኗል።

በዚህም መሰረት 65 እጩዎች ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት የቀረቡ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ የ55 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተካሂዷል።

ለማእከላዊ ኮሚቴ ከተመረጡት 55 ውስጥ 45ቱ ለኢህአዴግ ምክር ቤት አባልነት የሚቀርቡ ይሆናል።

ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት የተመረጡት ዝርዝርም በነገው እለት ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል።

ድርጅታዊ ጉባዔው በዛሬ ውሎው 12 ነባር አመራሮችንም በክብር አሰናብቷል።

በዚህም መሰረት፦

1 አቶ አባይ ወልዱ

2 ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ

3 አቶ ገብረመስቀል ታረቀኝ

4 አቶ ሚካኤል አብረሃ

5 አቶ ጎበዛይ ወልደአረጋይ

6 አቶ ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ

7 አቶ ነጋ በረኸ

8 አቶ ተወልደብርሃን ተስፋዓለም

9 አቶ ማሞ ገብረእግዚአብሄር

10 አቶ ጎይቶም ይብራህ

11 አቶ ሀይሌ አሰፈሃ

12 አቶ ኪሮስ ቢተው ከድርጅቱ በክብር ተሰናብተዋል።

የህወሃት ድርጅታዊ ጉባዔ በነገ ውሎው የድርጅቱን ሊቀ መንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ምርጫን እንዲሁም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን እንደሚያካሄድ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ምርጫ በማካሄድ በነገው እለት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በአብረሃም ሀይሌ

You might also like
Comments
Loading...