Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ሩዋንዳ ኪጋሊ ገባ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ሩዋንዳ ኪጋሊ ገብቷል፡፡

ቡድኑ ቅዳሜ በሚጀመረው እና በሩዋንዳ አስተናጋጅነት በሚካሄደው በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ላይ ለመሳተፍ ነው ኪጋሊ የገባው።

ኢትዮጵያን ጨምሮ 7 ሀገራት የሚሳተፉበት ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በምድብ አንድ ከኡጋንዳ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳን ጋር ተደልድሏል።

ቡድኑ ወደ ሩዋንዳ ያቀናው 20 ተጫዋቾችን አካቶ ሲሆን ለ10 ቀናት ይቆያል ተብሏል።

በዚህ ውድድር በ2021 በሞሮኮ አስናጋጅነት በሚካሄደው አህጉራዊ ከ17 ዓመት በታች እግር ኳስ ዋንጫ ቀጠናውን የሚወክሉ ብሔራዊ ቡድኖች እንደሚመረጡ ይጠበቃል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.