Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ቻይና አቀኑ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቻይና- አፍሪካ ትብብር ፎረም የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ቻይና አቀኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቻይና ቆይታቸው ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ ጋር በሀገራቱ መካከል ስላለው ግንኙነት ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።

በየ3 አመቱ በመሪዎች ደረጃ በሚካሄደው ጉባኤ፥ የአፍሪካ ሀገራት ከቻይና ጋር ባላቸው የምጣኔ ሃብት፣ የመሰረተ ልማት እና የማህበራዊ ዘርፎች ላይ ምክክር ያደርጋሉ።

በጉባኤው 10 የትብብር መስኮች የያዘውን የቤጂንግ ድንጋጌ በተመለከተና ለፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያነት በወጣው የድርጊት መርሃ ግብር አፈጻጸም ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በሚካሄደው በዚህ ፎረም በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ለመሳተፍ ወደ ቤጅንግ አቅንተዋል።

በሰላማዊት ካሳ

 

You might also like
Comments
Loading...