Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ“ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ” አማካሪ ምክር ቤት አቋቋሙ

የ“ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ” አማካሪ ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ“ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ” አማካሪ ምክር ቤት አቋቋሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸው እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በየቀኑ ቢያንስ 1 የአሜሪካ ዶላር በመለገስ ለተለያዩ የልማት ስራዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀው ነበር።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድን የሚያማክር ምክር ቤት ማቋቋማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል።

በዚህም መሰረት፦

 1. ዶክተር አለምአየሁ ገብረማርያም – የምክር ቤቱ ሊቀመንበር
 2. ዶክተር ብስራት አክሊሉ
 3. አቶ ገብርኤል ንጋቱ
 4. አቶ ካሳሁን ከበደ
 5. ዶክተር ለማ ሰንበት
 6. ወይዘሮ ሉሊት እጅጉ
 7. ዶክተር መና ደምሴ
 8. ወይዘሮ ሚሚ አለማየሁ
 9. አቶ ሚኒልክ አለሙ
 10. አቶ ኦባንግ ሜቶ
 11. አቶ ሮብሰን ኢታና
 12. አቶ ታማኝ በየነ
 13. አቶ ተሽታ ቱፋ
 14. አቶ ይሄነው ዋለልኝ እና
 15. አቶ ኤሊያስ ወንድሙ የምክር ቤቱ አባላት ተደርገው ተመርጠዋል።

ከዚህ ቀደምም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ተሳትፎ ለማቀናጀትና የልገሳውን ገንዘብ ለማሰባሰብ፥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በሚል ስም ሂሳብ መከፈቱም ይታወሳል።

የሂሳብ ቁጥሩም 1000255726725 ነው።

ገንዘቡን ለማስገባትም በቅርቡ ድረ ገጽ የሚከፈት ሲሆን እሱን በመቀጠም፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ስዊፍት አድራሻ እና CBETETAA እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን በመጠቀም ገንዘቡን መላክ እንደሚቻልም ተነግሯል።

You might also like
Comments
Loading...