Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ወርቅነህና አቶ ለማ በአስመራ የሚከፈተውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጎበኙ

ዶ/ር ወርቅነህና አቶ ለማ በአስመራ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በኤርትራ አስመራ የሚከፈተውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጎበኙ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በኤርትራ ከሚገኙት የኦነግ አመራሮች ጋር ለመደራደር ወደ አስመራ ባቀኑበት ወቅት ነው ኤምባሲውን የጎበኙት።

በጉብኝቱ ላይም የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳይሌን ጨምሮ ሌሎች የሀገሪቱ ባለስልጣናትም ተሳትፈዋል።

ከጉብኝቱ በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈውቂ ጋር በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ላይ ውይይት ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባሳለፍነው ሀምሌ ወር በተፈራረሙት የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰላምና የወዳጅነት ስምምነት ውስጥ የሁለቱን ሀገራት ኤምባሲ መልሶ መክፈት እንደሚገኝበት ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በኢትዮጵያ የኤርትራ ኤምባሲ ዳግም ተከፍቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ኤርትራ አዲስ አምባሳደር ወደ ኢትዮጵያ የመደበች ሲሆን፥ ኢትዮጵያም አዲስ አምባሳደር ወደ ኤርትራ መመደቧ ይታወሳል።

እንዲሁም ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን በቅርቡ በአስመራ ለመክፈት ዝግጅት እያደረኩ ነው ማለቷም አይዘነጋም።

ይህንን ተከትሎ ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በኤርትራ አስመራ የሚከፈተውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዛሬው እለት የጎበኙት።

You might also like
Comments
Loading...