Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር ከ6 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ብድር መስጠቱን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 10፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠቱን ገለፀ።

760 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች የብድሩ ተጠቃሚ መሆናቸውንም አክሲዮን ማህበሩ አስታውቋል።

ማህበሩ ከ9 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለመስጠት አቅዶ የነበረ ሲሆን፥ የዕቅዱን 70 በመቶ ማከናወን መቻሉንም ነው ያስታወቀው።

አፈጻጸሙ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 12 በመቶ ዕድገት እንዳለው አስታውቋል።

የገንዘብ ብድር ተጠቃሚ ከሆኑት ውስጥ አርሶ አደርና አርብቶ አደሮች፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ነዋሪዎች፣ ጥቃቅን አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተደረጁ፣ ተመራቂና ስራ አጥ ወጣቶች እንዲሁም በተዘዋዋሪ የወጣቶች ብድር ፈንድ ፕሮግራም የታቀፉ ወጣቶች ይገኙበታል።

በቁጠባ የተሰበሰበው የገንዘብ መጠን ከ5 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ሲሆን ከአምናው ጋር ሲነጻጸር 36 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል።

ማህበሩ የማበደር አቅሙን ለማጎልበትና ተደራሽነቱን ለማስፋት በአሁኑ ወቅት በአገልገሎት ላይ ከሚገኙት 333 ቅርንጫፎች በተጨማሪ 42 አዳዲስ ቅርንጫፎች መክፈቱን ማህበሩ አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

You might also like
Comments
Loading...