የቻይና ወታደራዊ ልምምድ አሜሪካን ለማጥቃት ኢላማ ያደረገ ነው ተባለ
ቻይና በ2017 ለወታደራዊ ወጪ 190 ቢሊየን ዶላር መመደቧ ተነግሯል
አዲስ አበባ፣ነሃሴ 11፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የቻይና የጦር ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች የሚያደርጉት ልምምድ አሜሪካና አጋሯቿን ኢላማ አድርጎ የሚከናወን መሆኑን ፔንታጎን አስታወቀ።
ይህ የአሜሪካ ቅሬታ የተሰማው ሁለቱ ሀገራት የንግድ ጦርነት በገቡበት ወቅት ሲሆን፥ ፔንታጎን ቻይና በአለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተፅዕኖ ለማሳደግ በ2017 ለወታደራዊ ወጪ 190 ቢሊየን ዶላር መመደቧን አስታውሷል።
ፔንታጎን በሪፖርቱ የቻይና ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች በቅርብ አመታት በአካባቢው የሚገኙ የውሃ አካላትን ለመቆጣጠርና አሜሪካና አጋሮቿን ኢላማ በማድረግ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አስታውቋል።
ሪፖርቱ ሀገሪቱ ያላትን አቅም የሚያሳይ ልምምድ ከማድረግ ባሻገር የቦምብ ጣይ አውሮፕላኖቹ ምን መልዕክት ለማስተላለፍ ልምምዱን አንደሚያደርጉ ግልፅ አይደለማ ብሏል።
ይህ የፔንታጎን ሪፓርት ይፋ የሆነው ሀገራቱ በመካከላቸው ያለውን የንግድ ጦርነት ለመፍታት ውይይት ለማደረግ በዝግጅት ላይ በሚገኙበት ወቅት ነው ተብሏል።
ምንጭ፦ Reuters