Fana: At a Speed of Life!

እጅን መታጠብ

እጅን መታጠብ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) እጅን መታጠብ በሽታ  የሚያመጡ ጀርሞችን ተከላክሎ ከበሽታ ለመጠበቅ ተመራጭ መፍትሄ ነው፡፡

እጅን በሳሙና ጣቶች መሃል እና ጥፍር ስር በማሸት መታጠብ እና  በንፁህ ፎጣ ማድረቅ ተገቢ ነው፡፡

ጀርሞች በተለያዩ መንገዶች ይሰራጫሉ፡፡

  • ቆሻሻ እጅን በመንካት
  • የህፃናት የቆሸሸ ጨርቅ ሲቀየር
  • በተበከለ ውሃ እና ምግብ
  • በሳልና በማስነጠስ
  • በህመምተኛ የሰውነት ፈሳሽ ንክኪ

እጅን በደንብ መታጠብ ደግሞ በእነኚህ ጀርሞች የሚተላለፉ  ብዙ  በሽታዎች ( ተቅማጥ፣ ጉንፋን፣ ጉበት  እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች) የመጀመሪያው መከላከያ መፍትሄ ነው፡፡

እጅን

  • ከመብላትና ከማብሰል በፊት
  • መፀዳጃ ቤት ከተጠቀምን በኋላ
  • ቤት ከማፅዳት በኋላ
  • እንስሳትን ከመንካት በኋላ
  • የታመመ ሰው ከመጎብኘት እና ከመርዳት በፊት እና በኋላ  እና ከሌሎች መሰል ጥንቃቄ ከሚፈልጉ ሥራዎች በፊት እና በኋላ መታጠብ ጤናን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡

ምንጭ፡- https://kidshealth.org

 

You might also like
Comments
Loading...