Fana: At a Speed of Life!

ሳዑዲ መራሹ ጦር በየመን በወሰደው የአየር ጥቃት 12 አሳ አስጋሪዎች ተገደሉ

በሆዳይዳ ግዛት የሚኖሩት አሳ አስጋሪዎች  በግዛቷ እየተካሄደ  ባለው ግጭት ምክንያት አካባቢውን ለመልቀቅ እየተገደዱ መሆኑ ታውቋል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በየመን ሆዴኢይዳ ግዛት  ሳዑዲ መራሹ ጦር በወሰደው የአየር  ጥቃት 12 አሳ አስጋሪዎች መገደላቸው ተነገረ።

ሆኖም ሳዑዲ መራሹ ጦር ጥቃት የተሰነዘረባት መርከብ የጦር መሳሪያ የጫነች መሆኑን አስታውቋል።

በሆዴኢይዳ ግዛት የሚኖሩት አሳ አስጋሪዎች  በግዛቷ እየተካሄደ  ባለው ግጭት ምክንያት አካባቢውን ለመልቀቅ እየተገደዱ መሆኑ ታውቋል።

ሳዑዲ መራሹ ጦር በሀውቲ አማፂ ቡድን ቁጥጥር ስር የምትገኘውን ይህችን ከተማ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በቅርቡ በተመሳሳይ ሳዑዲ መራሹ ጦር በወሰደው የአየር ጥቃት 28 ሰዎች ህይወት እንዳለፈና 30 የሚሆኑን የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚታወስ ነው።

ምንጭ፥ አልጀዚራ

You might also like
Comments
Loading...