Fana: At a Speed of Life!

ለመስቀል አደበባይ የቦንብ ጥቃት ተጎጂዎች የህክምና ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት የእውቅናና የምስጋና መድረክ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ ነሃሴ 13፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ በመስቀል አደበባይ ሰኔ 16 በደረሰው የቦንብ ጥቃት ለተጎዱ ወገኖች የህክምና ድጋፍ ላደረጉ የመንግስት የህክምና ተቋማት የእውቅናና የምስጋና መድረክ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

በዚሁ የእውቅናና የምስጋና መድረክም ለ13 የመንግስት የጤና ተቋማት የምስጋና ወረቀትና የአምቡላንስ ቁልፍ መበርከቱ ነው የተገለጸው።

በስነስርአቱ ላይ የተገኙት የጤና ጥብቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን የጤና ተቋማቱ ላበረከቱት አስትዋጽኦ ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል።

ባለፈው አመት የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል 3 ሺ ዘመናዊ አምፑላንሶችን ለመግዛት ቢታቀድም ተገዝቶ ለክልሎች የተከፋፈለው ግን 1 ሺ 3 መቶ ብቻ መሆኑን የገለጹት ዶክተር አሚን በጤና ተቋማት የሚሰጠው የድንገተኛ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ሊሻሻል እንደሚገባም አመላከተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የከተማ አስትዳደሩ በአምቡላንስ አገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቅረፍ አስፈላጊው ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በሲሳይ ሃይሌ

You might also like
Comments
Loading...