Fana: At a Speed of Life!

ፓኪስታናውያን ኢምራን ካን ከጠቅላይ ሚኒስትነትር መነሳታቸውን በመቃወም አደባባይ ወጡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በርካታ ቁጥር ያላቸው ፓኪስታናውያን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን ከስልጣን መነሳታቸውን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ እያደረጉ ነው፡፡
የሀገሪቱን ዋና ከተማ ኢስላምባድን ጨምሮ በርካታ የፓኪስታን ከተሞች በከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ እየተናጡ ነው ተብሏል፡፡
ኢምራን ካን “የፓኪስታን ህዝብ ከውጭ በመጣ አጭበርባሪ መንግስት ላለመገዛት በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ ለተቃውሞ ወጥቷል” በማለት የተቃውሞ ሰልፉን ፎቶ አስደግፈው በትዊተር ገጻቸው አጋርተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ካን ÷ “በሩሲያ እና ቻይና ጉዳይ ድጋፍ ባለማሳየቴ አሜሪካ ከሥልጣን እንድነሳ ጽኑ ፍላጎት አላት፤ የሃገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ከውጭ ኃይሎች ጋር አብረው እየሠሩ ነው” ሲሉ በተደጋጋሚ መናገራቸው ይታወሳል።
አሜሪካ በበኩሏ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ውንጀላ መሰረተ ቢስ ነው ማለቷን አር ቲ ዘግቧል፡፡
ካን የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ሞስኮ ሄደው ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር መገናኘታቸው በአሜሪካ በክፉ እንዲታዩ ሳያደርጋቸው አልቀረም የሚሉም አሉ፡፡
የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን በሀገሪቱ ፓርላማ የመተማመኛ ድምጽ ማጣታቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.