Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር በላቸው መኩሪያ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ዶክተር በላቸው መኩሪያ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በምክትል ኮሚሽነርነት ሲሰሩ የነበሩት ዶክተር በላቸው መኩሪያ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሆነው እንደተሾሙ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ነው ያስታወቀው።

ሀገሪቱ በኢንቨስትመንት ዘርፉ የፈጠረቻቸውን መነቃቃቶችና መልካም ጅምሮች ማስቀጠል ቀዳሚ ስራቸው እንደሚሆንም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ከኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር በመሆን አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋትና አለም አቀፍ ልምዶችን በመቅሰም ኮሚሽኑን አለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ ለማድረግም እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

ዶክተር በላቸው ላለፉት ሁለት አመታት የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ሲሰሩ መቆየታቸው ተነግሯል።

ኮሚሽኑን ላለፉት ዓመታት በኮሚሽነርነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ፍጹም አረጋ የጠቅላይ ሚኒስቴር ልዩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው እንደተሾሙም ታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

You might also like
Comments
Loading...