Fana: At a Speed of Life!

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ማትረፉን አስታወቀ

 አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በግማሽ አመቱ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ማትረፉን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር አስታወቀ።ትርፉን በስሩ በሚገኙ የልማት ድርጅቶች ምርትና አገልግሎት ማግኘቱንም አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ረዳት ሃላፊ አቶ አሰበ ከበደ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የልማት ድርጅቶቹ ባደረጉት አፈጻጸም 1 ቢሊየን 445 ሚሊየን 975 ሺህ ብር ማትረፍ መቻሉን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን፣ የህንጻ እቃዎች አቅራቢ ድርጅት እና ብሄራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ለትርፉ ከመቶ ፐርሰንት በላይ አፈጻጸም ያሳዩ ናቸው ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ በግማሽ አመቱ ከምርትና አገልግሎት ሽያጭ 18 ቢሊየን 390 ሚሊየን 588 ሺህ ብር ገቢ ማግኘቱንም ገልጸዋል።

ይህም ከእቅዱ አንጻር 72 በመቶ አፈጻጸም አለው ብለዋል።

 

በታሪክ አዱኛ

You might also like
Comments
Loading...