Fana: At a Speed of Life!

ሳንባችን በ72 ስዓታት የምናፀዳበት መንገድ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ)በርካታ ሲጋራ አጫሾች ለተለያዩ በሽታዎች ይጋለጣሉ፤ ከምንም በላይ ግን ሲጋራ የሚጎዳው ሳንባችንን ነው።ጥቂት የማይባሉ ሲጋራ የማያጨሱ ሰዎችም ሳንባቸው ሲጎዳና ለህመም ሲዳረጉ ይስተዋላል።

እኛም በ72 ስዓታት ወይንም በሶስት ቀናት ሳምባችንን ንፁህ እና ጤናማ ለማድረግ የሚረዱ ነጥቦችን እንጠቁማችሁ።

ቀጥለን በምናያቸው እና ለሶስት ቀናት ደጋግመን ብንተገብራቸው ከሚመከሩ ነገሮች ውስጥ ከወተትና ወተት ነክ ምግቦች መራቅ ዋንኛው ነው።

1. በመጀመሪያው ቀን ሳንባችንን ንፁህና ጤናማ የማድረግ ስራችን፥ ከመኝታ በፊት 1 ኩባያ ሻይ መጠጣት ይመከራል፤ ይህም የሆድ ድርቀትን የሚያስከትሉ ጎጂ ነገሮችን ያስወግዳል።

2. ከቁርስ በፊት የተጨመቀ 2 ሎሚ ከ300 ሚሊ ሊትር ውሃ ጋር በማደባለቅ መጠጣት፣

3. ከዚያም 300 ሚሊ ሊትር የፍራፍሬ ጨማቂ አልያም የአናናስ ጭማቂ መጠጣት ተገቢ ነው፤ ሁለቱም የጭማቂ አይነቶች የያዙት ተፈጥሯዊ አንቲኦክሲዳንትስ የአተነፋፈስ ስርዓታችንን ለማሳደግ ይረዳል።

4. በቁርስና ምሳ ስዓት መካከል 300 ሚሊ ሊትር የካሮት ጭማቂ መጠጣትም አስፈላጊ ነው ተብሏል፤ ይህ ጭማቂ በ72 ስዓታት ውስጥ ደማችን አልካላይዝ እንዲሆን ይረዳል።

5. ምሳ ስዓት ላይ ደግሞ በፖታሲየም የበለፀገ 400 ሚሊ ሊትር ጭማቂ መጠጣት የሚኖርብን ሲሆን፥ ይህም ፖታሲየም ሳንባችንን የማፅዳቱን ተግባር እንዲያፋጥን ያደርገዋል።

6. ወደ መኝታችን ከማምራታቸን በፊትም 400 ሚሊ ሊትር የእንጆሪ ጭማቂ መጠጣት ለሳንባ ኢንፌክሽን የሚዳርጉ ባክቴሪያዎችን ለመከላከል ከፍተኛ ድርሻ አለው።

7. በእነዚህ ቀናት ሞቅ ባለ ውሃ ለ20 ደቂቃ ሻወር መውሰድም በርካታ ተህዋሲያን እንዲወገዱ ይረዳል።

8. በሞቀ የሻወር ገንዳ ከ5 እስከ 10 የባህር ዛፍ ቅጠል በመበተን ጭንቅላታችንን በጨርቅ በመሸፈን ውሃው እስኪቀዘቅዝ ድረስ መተንፈስ፤ ከላይ የጠቀስናቸውን ነገሮች ለተከታታይ ሶስት ቀናት በተደጋጋሚ መተግበር ይገባል።

በዚህ ሳምባችንን በምናክምበት ወቅትም ከከባድ ስራ መራቅ ይኖርብናል።

ምንጭ፦ naturalcuresnotmedicine.com

You might also like
Comments
Loading...