Fana: At a Speed of Life!

ዩኒሴፍ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የህጻናት አድን ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የተሟላ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡

የድርጀቱ የምስራቅና የደቡብ አፍሪካ ቀጠናዊ ቢሮ የህጻናት ጥበቃ ሪጅናል አማካሪ አንደሪው በሮክስ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስተር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም÷ መንግስት በተከሰተው ጦርነት እና በድርቅ ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችንና የተፈናቀሉ ወገኖችን የመደገፍና የማቋቋም ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ዶክተር ኤርጎጌ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ ከዩኒሴፍ ጋር ለረጅም ጊዜያት ያላትን ውጤታማ ግንኙነት ለማጠናከር እንዲቻል በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና በድርጅቱ በኩል የሚከናወኑ ድጋፎችን ሳያደራርቡ አቀናጅቶ ለተጎጂዎች ተደራሽ በማድረግ ትክክለኛ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የድርጅቱን ለረጅም ጊዜ የቆየ ድጋፍና ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ያደነቁት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ÷ በቀጣይም ድርጅቱ ያለውን የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

የዩኒሴፍ ሪጅናል አማካሪ አንደሪው ብሮክስ ÷ በግጭቱና በድርቁ ምከንያት የተጎዱ አከባቢዎችንና የህብረተሰብ ከፍሎችን ለመደገፍና ከዚህ በፊት ከነበረው የላቀ ለማድረግ የተሟላ የድጋፍ አገልግሎትና ቅንጅታዊ ስራዎች በድርጅቱና በመንግስት በኩል ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ዩኒሴፍ በአሁኑ ወቀት ድጋፎችን እያከናወነ የሚገኘ ሲሆን÷ በቀጣይም በግጭቱና በድርቁ ምክንያት የተጎዱ አከባቢዎችን የመደገፍ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣ለህጻናት የአልሚ ምግብ ድጋፍ የማድረግ፣ በህጻናት ድጋፍና ጥበቃ ዙሪያ ተዓማኒ መረጃ እንዲኖር የተደራጀ ሲስተም የመፍጠር እቅድ መያዙ ተገልጿል፡፡

በችግር ውስጥ የሚገኙ ህጻናትን ለመደገፍ እንዲቻል የኬዝ ማኔጀመንት ስራን የማከናወን እና የማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችን መድቦ የተለያዩ የማህበራዊና የስነ-ልቦናዊ ድጋፍ በጦርነቱ ለተጎዱ ህጻናትና ሴቶች የመስጠት ስራን ለማከናወንም ድርጅቱ ቃል ገብቷል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.