Fana: At a Speed of Life!

የጣሊያን ሎምባርዲያ ክልል ፕሬዚዳንት ባለሐብቶቻቸው በኢትዮጵያ መዋዕለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ እንደሚያበረታቱ ጠቆሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በሀገሪቷ ከሎምባርዲያ ክልል ፕሬዚዳንት አቲሊዮ ፎንታና ጋር በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝምና ንግድ ዙሪያ በጋራ መሥራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውን ገለጹ።
በውይይቱ አምባሳደሯ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እንዳብራሩና ያለውን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጭ እንዳስረዱ ጠቁመዋል፡፡
በሎምባርዲያ የሚገኙ ባለሐብቶችም በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ እንዲሳተፉ ፕሬዚዳንቱ ድጋፍ እንዲያደርጉ አምባሳደር ደሚቱ ጠይቀዋል።
የሎምባርዲያ ፕሬዚዳንት በበኩላቸው ÷ በሎምባርዲያ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ የሚችሉ በርካታ ባለሐብቶች እንዳሉ ጠቅሰው በአምባሳደሯ የቀረበውን ሃሳብ እንደሚቀበሉት አስታውቀዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ሌሎች መስኮች ላይ በትብብር ለመሥራት መሥማማታቸውን በሮም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.