Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱበት ጊዜ አሁን ነው – ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣መጋቢት 14፣2014(ኤፍ ቢሲ) በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የውጭ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሚ ተናገሩ፡፡
ከሚሽነሯ ሪሞርቺያቶሪ ሪዩኒቲ ከተባለው የጣሊያን የባህር ትራንስፖርት ኩባንያ ቡድን ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
ኮሚሽነሯ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት በጣሊያን ግንባር ቀድም ከሆነው ኩባንያ ጋር በሎጂስቲክስ ዘርፍ ቀጣይ የኢንቨስትመንት እቅዶቻቸው እና ተግባሮቻቸው ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።
ሪሞርቺያቶሪ ሪዩኒቲ ኩባንያ ቀደም ሲል ከትራነስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ጋር ውይይት ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡
በዚህ ወቅትም በባህር ትራንስፖርት ዘርፍ በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው መግለጹ የሚታወስ ነው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.