የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሁመራ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጣረ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የህውሓት ቡድን ከጠላት ጋር ጥምረት በመፍጠር ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት የነበረውን የሁመራ አውሮፕላን ማረፊያን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።
በስሜን እዝ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሙሉ አለም አድማሱ፥ መከላከያ ሃይሉ የተፈፀመበትን ታሪካዊ ክህደት እና ጥቃት አክሽፎ ሁሉን አቀፍ ጥቃት እያካሄደ ነው ብለዋል።
ህግ የማስከበር ኦፕሬሽኑን በድል እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በምእራብ ትግራይ በኩል ህግ የማስከበር እርምጃ እየወሰደ ያለው የኢፌዴሪ መከላከያ ሃይል እስካሁን የህወሓት ታጣቂ ቡድን ስፍሮባቸው የነበሩ ከተሞችን ሙሉ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥራል።
በርካታ ህውሓት ያደራጃቸው የልዩ ኃይል፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን እየሰጡ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
በዚህም የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት እስካሁን ማይዳሊ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ ልጉዲ እንዲሁም የሁመራ ሱዳን መንገድን እንደተቆጣጠረ መቆጣጠሩ ይታወቃል።