Fana: At a Speed of Life!

የኢድ- አል ፈጥር በዓልን ለማክበር ወደ ክልሉ የሚመጡ እንግዶችን በድምቀት ለማስተናገድ ተዘጋጅተናል- የሀረር ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢድ- አል ፈጥር በዓልን እንዲሁም በክልሉ በልዩ ሁኔታ የሚከበረውን የሸዋል-ኢድ በዓልን ለማክበር ወደ ሀረር የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት÷ መጪውን የኢድ- አል ፈጥርና ሸዋል-ኢድ በአላትን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት ተደርጓ፡፡
በተለይም ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው የኢድ- አል ፈጥርና ሸዋል-ኢድ በአላትን ለማክበር ከተለያዩ የአለም ሀገራትና የሀገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል በሚከናወኑ ተግባራት የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የክልሉ ህዝብም ለበአሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ቤቱን ክፍት አድርጎ መጠበቅ እና በአሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በጋራ መንቀሳቀስ እንደሚገባው መናራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.