የአሸባሪው ህወሓትን ሀገር የማፍረስ ሙከራ ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ለመከቱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ልዩ ኃይል አባላት አቀባበል ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዳሴ ግድብ ጥበቃና አሸባሪው ህወሓት የፈፀመውን ሀገር የማፍረስ ሙከራ ከመከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የመከቱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝች ክልል ልዩ ኃይል አባላት በቦንጋ ከተማ አቀባበል ተደረገላቸው።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በአቀባበል መርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ አሸባሪው ህወሓት የኢትዮጵያን አንድነትና ሰላም ለማናጋት የከፈተውን ጦርነት ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ሆናችሁ በመቀልበሳችሁ የክልሉ መንግስትና ሕዝብ ኩራት ተሰምቶታል ብለዋል፡፡
በቀጣይም የክልሉን ሰላም አስተማማኝ በማድረግና በሌሎች ተልዕኮዎች ላይ ከየትኛውም ወገንተኝነት በፀዳ ሁኔታ ተልዕኳችሁን በስኬት እንድትወጡ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነብዩ ኢሳያስ÷ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት እንደ ሀገር የተሰጣችሁን ተልዕኮ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለፈፀማችሁት ውጤታማ ተግባር እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ በበኩላቸው÷ በጀግንነት የከፈላችሁት መስዋዕትነት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው ብለዋል፡፡
በዓለማየሁ መቃሳ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!