Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ምክትል ዳይሬክተር በአማራ ክልል እየተደረጉ ያሉ የመልሶ ግንባታ ሥራዎችን ተመለከቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) የኢትዮጵያ ምክትል ዳይሬክተር ጂም ዶብሰን አሜሪካ በምሥራቅ አማራ አካባቢዎች በመልሶ ግንባታው ላይ የምታደርገውን ድጋፍ ተመለከቱ፡፡
ምክትል ዳይሬክተሩ በጉብኝታቸው÷ የተራድኦ ድርጅቱ የማሕበረሰብ አገልግሎቶችን እየደገፈ የሚገኝባቸውን መጋዘኖች፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እና ጤና ጣቢያዎችን ተመልክተዋል፡፡
በግጭቱ በተጎዱ አካባቢዎች እና ማሕበረሰቦች ላይ እየተካሄደ ስላለው የማገገሚያ ጥረት ከተማሪዎች፣ ከማህበረሰብ መሪዎች፣ ከጤና ባለሙያዎች እና ከአካባቢው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.