Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ቤጂንግ የበጋ ኦሎምፒክ ውድድሮች ዓለምአቀፋዊ አንድነትን እና ትብብርን አጠናክረዋል – ሺ ጂንፒንግ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና አለመረጋጋቶች በሰፈኑበት ወቅት የቤጂንጉን የኦሎምፒክ እና ፓራ-ኦሎምፒክ ውድድሮች በብቃት ማስተናገድ መቻሏ በራስ መተማመንን፣ ተሥፋን እና አንድነትን ለዓለም ያመጣ ክስተት መሆኑን የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ገለጹ፡፡

ሺ ጂንፒንግ ÷ በትናንቱ ጉባዔ ለኦሎምፒኮቹ መሳካት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ሽልማት ሰጥተዋል፡፡

ሽልማቶቹ የተሰጡትም በጨዋታዎቹ በ148 ስምሪቶች ውስጥ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው አካላት እና በጨዋታው የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ 148 ግለሰቦች መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በውድድሮቹ የታየው መንፈሥ በቤጂንጉ ኦሎምፒክ እና ፓራሊምፒክ የሚቆም ሳይሆን ነገ ለሚፈጠረው የተሻለ ዓለም ተሥፋ ሆኖ ይቀጥላልም ነው ያሉት – ሺ፡፡

በውድድሩ በጠቅላላ 346 ሚሊየን ቻይናውያን እንደተሳተፉበት እና ቤጂንግ ባደረገችው ከፍተኛ የመከላከል እና የመቆጣጠር ዘመቻ ከተሳታፊዎች 0 ነጥብ 45 በመቶ ያህሉ ብቻ የኮቪድ 19 ቫይረስ እንደሆኑ ሲጂቲ ኤን በዘገባው አመላክቷል፡፡

ቻይና ከሰባት ዓመታት ጥረት በኋላ በፈረንጆቹ 2022 ባሳለፍነው የካቲት እና መጋቢት ወራት የበጋ ኦሎምፒክ እና ፓራ-ኦሎምፒክ ውድድሮችን በስኬት ማስተናገድ ችላለች፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.