Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ጦር በዩክሬን በሚያካሂደው ወታደራዊ ዘመቻ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ህጎችን በጥብቅ ያከብራል-ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ወታደሮች በዩክሬን በሚያካሂዱት ወታደራዊ ዘመቻ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ህጎችን በጥብቅ እንደሚያከብሩፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ፡፡
 
ፕሬዚዳንት ፑቲን ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና ከጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በስልክ ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደች ባለው ወታደራዊ ዘመቻ እና ጦርነቱን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የምግብ ቀውስ ዙሪያ በትኩረት መክረዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንት ፑቲን የሩሲያ ወታደሮች በዩክሬን በሚያካሂዱት ወታደራዊ ዘመቻ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ህግጋትን በጥብቅ እንደሚያከብሩ አስገንዝበዋል፡፡
 
አሁን ላይ መቀዛቀዝ የታየበትን የሩሲያ-ዩክሬን የሰላም ድርድር ለማስቀጠል ሞስኮ በሯ ክፍት መሆኑንም ነው ፕሬዚዳንት ፑቲን የገለጹት፡፡
 
ምዕራባውያን ለዩክሬን የሚያቀርቡት የጦር መሳሪያ እርዳታ የተጀመረውን ጦርነት ይበልጥ ከማባባሱ ባለፈ በቀጣይ በቀጠናው የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል።
 
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የምግብ እጥረት ዋነኛ መንስኤው ምዕራባውያን የሚከተሉት የተዛባ የኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ፖሊስ ውጤት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
 
የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍም ሩሲያ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የምግብ እህል ወደ ውጪ ለመላክ ዝግጁ ናት ማለታቸውን ሺንዋ ዘግቧል።
 
ወደ ውጪ የሚላኩ የግብርና ምርቶችን እና የአፈር ማዳበሪያ መጠን መጨመር የተፈጠረውን ቀውስ ለማረጋጋት ያስችላል ያሉት ፕሬዚዳንት ፑቲን፥ ለዚህም ምዕራባውያን በተያያዥ ጉዳዮች ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ማንሳት ይገባቸዋል ብለዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.