Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላትን አመሰገኑ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ።

“ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ መላው የከተማችን ነዋሪዎች ላሳያችሁት ፍፁም ኢትዮጵያዊ እንግዳ ተቀባይነትና አክባሪነት ልባዊ ምስጋናችንን እና አድናቆታችንን ለመግለፅ እንወዳለን” ብለዋል ከንቲባዋ።

ጉባኤው ለኢትዮጵያ የተለየ ትርጉም እንዳለው በመረዳት አካባቢያቸውን በማፅዳት፣ ከተማውን በማስዋብ፣ በመብራት በማድመቅ እና በተለያየ አፍሪካዊ እሴቶች በማሸብረቅ ለጉባኤው ድምቀት በልዩ ሃገራዊ ስሜት ሃላፊነታቸውን ለተወጡ የግልና የመንግስት ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል።

በየደረጃው የሚገኙ የከተማዋ አመራሮች፣ የፀጥታ ሃይሎች ፣ ለፕሮግራሙ ስኬት የተባበሩና የተሰማሩ ተቋማትና ድርጅቶች ጉባኤው በሰላም ተጀምሮ ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት አስተዋፅኦም እንዲሁም ወይዘሮ አዳነች አመስግነዋል።

በጉባኤው ወቅት የታየው ህብረትና አንድነት  ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ነው ጥሪ ያቀረቡት።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.