Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ታከለ በማዕድን ኢንቨስትመንት ዙሪያ ከእንግሊዝና አውስትራሊያ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከእንግሊዝ አምባሳደር ዶክተር አላስታይር ማችፌል እና ከአውስትራሊያ አምባሳደር ጁሊያ ኒብሌት ጋር ተወያዩ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት ፥ በውይይታቸው በማዕድንና በተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋና ምርት ላይ በተሰማሩ የእንግሊዝ እና የአውስትራሊያ ኩባንያዎች የስራ እንቅስቃሴ ላይ አተኩረዋል፡፡

የእንግሊዝ እና የአውስትራሊያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንት ላይ በሰፊው የሚሳተፉበት መንገድ ላይም ከአምባሳደሮቹ ጋር ውይይት ማድረጋቸውንም ነው የገለጹት፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.